ጉዳዮች

ዲሲ ባለጠጋ እና ፍትሐዊ ከተማ ልትሆን የገባል፡፡ እዚያ እንድንደርስ ደግሞ የእኔ ራዕይ ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡

Seven Point Plan to Prevent Violence

የሕዝብ ደህንነትን ለማረጋገጥ አሁን ያለው ሁኔታ የማያስኬድ በመሆኑ በግልጽ እየታየ እንደመሆኑ መጠን አዲስ አካሄድ መከተል ይኖርብናል፡፡ ወንጀልን በመከላከል እና ወደ ኃይል ድርጊት ለሚያመሩ ሁኔታዎች መፍትሔ ካገኘን፣ ከተማችን ይበልጥ ለደህንነት ምቹ ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ፍትሐዊ እንድትሆን ማድረግ እንችላለን፡፡

መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ

ያደግሁት በዲሲ ነው፤ ነገር ግን እንደ በርካታ የዲሲ ቤተሰቦች ሁሉ ለእኔም ቤተሰብ ለ25 ዓመታት የኑሮ ዋጋ ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ ላጋጠመን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ፈጠራ የተሞላባቸው መፍትሔዎች በማበጀት፣ የመፈናቀልን ማዕበል እንቀለብሳለን፤ በዲሲ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ በዲሲ መኖር መቻላቸውን እናረጋግጣለን፡፡

ለሁሉም ተማሪዎች የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች መፍጠር

አሁን ያለውን የትምህርት ሁኔታ መቀበል አንችልም፤ ቤተሰቦች በበርካታ ቁጥሮች የዲሲን የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለቅቀው በመውጣት ላይ ናቸው፤ እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ወደ ኋላ እየቀሩ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ትምህርት ቤቶቻችን የሚያስልጓቸውን ኃብቶች ሁሉ ሲያገኙ፣ በትምህርት ክፍል ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ከተማችን ውስጥ የማይታመኑ ውጤቶችን እናያለን፡፡

እምነታችንን ልንጥልበት የምንችል የአካባቢ አስተዳደር መፍጠር

በመንግሥታችን ላይ ያለንን እምነት እና መተማመን መልሰን መገንባት አለብን፤ ይህ ነገር ለባለጠጎች እና ለባለ ዘመዶች/ወዳጆች በአንድ መንገድ ሲሰራ ለሌሎቻችን ደግሞ የሚሰራው በሌላ መንገድ ነው፡፡ ተጠያቂ፣ ግልጽ እና ሰው ተኮር የመንግሥት ባሕል ስንፈጥር፣ ሰዎች በመንግሥታቸው በድጋሚ ለማመን ምከንያት እንሰጣቸዋለን፡፡

ጠንካራ የሥራ ኃይል መገንባት

ሁሉም ነዋሪዎቻችን እያደገ ከመጣው የከተማችን ብልጽግና መቋደስ መቻል አለባቸው፤ ይህም ሆኖ ዲስትሪክቱ ነዋሪዎቻችንን፣ በተለይ ደግሞ ባለቀለም ቆዳ ነዋሪዎች በኢኮኖሚው ውስጥ ስፍራ እንዲያገኙ ለማገዝ አልቻለም፡፡ የሥራ ሥልጠናችንን ለማሻሻል ተጨባጭ ኢንቬስትመንቶች በማድረግ ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች በከተማዪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተደራሽ ትራንስፖርት

ልናስቀረው የምንችለው የሞት አደጋ ከተከሰተ በኋላ ለእያንዳንዱ ክስተት እና ለየክስተቱ ምላሽ መስጠት ብቻ ሳይሆን በከተማችን ትራንስፖርት እንዲኖር ራዕይ የሞላው ዕቅድ ይዘን መስራት አለብን፡፡ ተደራሽነትን፣ ቀጣይነትን እና ደህንነትን በተመለከተ ቀጥተኛ ኢንቬስትመንት በምናደርግበት ጊዜ፣ ደህንነታቸው ለተጠበቀ መንገዶች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚቀርብ የሕዝብ ትራንስፖርት እና ለአካባቢያዊ ውጤታማነት እንደ ሞዴል የምንወሰድ አስተዳደር እንሆናለን፡፡

አካባቢያችንን መጠበቅ

አካባቢያዊ ቆጣቢነትን እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ከተማችን ሥርዓታዊ አቀራረብን መከተል የነበረባት ጊዜ አልፏል፡፡ ቁርጠኛ ከሆንን፣ ዲሲ በታዳሽ ኤነርጂ፣ በአካባቢ ደህንነት እና ቀጣይነት ባለው መሠረተ ልማት መሪነትን ትጨብጣለች፡፡ የፕላኔታችንን እና የነዋሪዎቻችንን ጤና እንጠብቃለን፡፡

ሥነ ጥበባችንን እና ባሕላችንን ስለመጠበቅ

በርካታ ነዋሪዎች ከተማችን ይበልጥ ባለጠጋ እየሆነች በሄደች ቁጥር፣ ዲሲን ዲሲ የሚያደርጓትን ባሕሎች እያጣን ሄደናል ብለው ይጨነቃሉ፡፡ ወደዚህ ከተማ የሚዘዋወሩ አብዛኞቹ ሰዎች በባሕላችን ፍቅር ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ባሕላችንን ወደ ጎን ከመውደቅ ለማዳን የአካባቢያችንን የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ማገዛችንን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ለሥነ ጥበብ ማኅበረሰባችን ኢንቬስትመንት እና ድጋፍ መስጠት እንችላለን፤ በዚህም መልኩ የዲሲ ባሕል ሕልውናውን ይዞ እንዲቀጥል ብቻ ሳይሆን ማሳደግም እንችላለን፡፡

ንቁ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን መመስረት

ከተማችን እያደገች ስትሄድ፣ የአነስተኛ ንግድ ሥራ ማኅበረሰባችንም ማደጉን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ማነቆውን ስናስወግድ እና በአናሳዎች እና በሴቶች ባለቤትነት የተያዙ የንግድ ድርጅቶችን ስንደግፍ፣ የአነስተኛ ንግድ ዘርፋችን ብዝሃነት እያገኘ እና እያደገ ይሄዳል፤ ብዙዎች ተጨማሪ የዋሽንግተን ነዋሪዎችም የአንትረፕረነርሺፕ ህልማቸውን ለማሳካት ይችላሉ፡፡