የምታምኑትን የአካባቢ መንግሥት መፍጠር

በመንግሥታችን ላይ ያለንን እምነት እና መተማመን መልሰን መገንባት አለብን፤ በአሁኑ ወቅት የዲሲ መንግሥት ለባለጠጎች እና ለባለ ዘመዶች/ወዳጆች በአንድ መንገድ ሲሰራ ለሌሎቻችን ደግሞ የሚሰራው በሌላ መንገድ ነው፡፡ ከመንግሥት ኤጀንሲዎች አነስተኛ አገልግሎትን ማመስገን ለምደናል፤ ፖለቲካ አስተዳደርን ሲጋርድ እንዲሁ መመልከትን ተላምደናል፡፡

የመንግሥትን ተጠያቂነት አበክሬ የምከታተል ሆኜ ቆይቻለሁ፤ ለተሻለ አፈጻጸም ጥረት ሳደረግ እና የግብር ከፋይን ገንዘብ በተሻለ ኃላፊነት ወጪ ለማድረግ ግፊት ሳደረግ ቆይቻለሁ፡፡ ኤጀንሲዎች የመንግሥትን ገንዘብ እና ንብረት ያለ አግባብ ሲጠቀሙ ፊት ለፊት ተናግሬያለሁ፡፡ መንግሥታትን ስለሚሰራበት መንገድ በቀጥታ ለመመልከት እና የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ቀጥተኛ ግንዛቤ እንዲኖረኝ ቅድሚያ ሰጥቼ የምሰራበት ነው፡፡

ሰዎች በመንግሥታቸው የሚያምኑበት ምክንያት ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህም የሚጀምረው ተጠያቂነት ካለው፣ ከግልጽ እና በሰዎች ላይ ከተመሠረተ የመንግሥት ባህል ነው፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደመሆኔ መጠን የሚከፈሉትን እፈጽማለሁ፡-

  • ከፍተኛው አመራር ከፍ ያለ ስታንዳርድ እንዲያከብር ማድረግ እና ተጠያቂነትን መጠየቅ፤
  • ከሁሉ የተሻሉት እና ብሩሆቹ፣ ተገቢው የትምህርት ዝግጅት እና ልምዱ ያላቸው እንዲሁም ሕዝብን ለማገልገል ቁርጠኛ የሆኑት የኤጀንሲ ኃላፊዎች ሆነው እንዲያገለግሉ መመደብ፤
  • በመንግሥት መሠረተ ልማት ውስጥ የውስታዊ ሥነ ምግባር መጠበቂያዎች ማበጀት፤
  • ከዲሲ ምክር ቤት ጋር በተሻለ ግልጽነት እና ትብብር መስራት፤
  • የግብር ዶላርን በማኅበረሰባችን ውስጥ ለማስቀረት ተጨማሪ የመንግሥት ውሎች ወደ አካባቢ የንግድ ድርጅቶች እንዲሄድ ማድረግ፤
  • ሕዝቡ መንግሥትን ተጠያቂ እንዲያደርግ ግልጽ ግቦች ማስቀመጥ፤