መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ

እንደ ሌሎች በርካታ የዋሽንግተን ነዋሪዎች ሁሉ፣ ለእኔም ቤተሰብ የዲሲ የኑሮ ዋጋ ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ የኪራይ ዋጋ እየጨመረ በመሆኑ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሊቀርብ የሚችል መኖሪያ ቤት እጅግ አነስተኛ ስለሆነ፣ ለአዲስ መጪ ነዋሪዎች በከተማዪቱ መኖር አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይም ቤተሰቦች ሊያድጉ የሚችሉባቸውን ቤቶች ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡ 

በምክር ቤቱ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የተሻሉ መኖሪያ ቤቶች እንዲቀርቡ ስጣጣር ቆይቻለሁ፤ ለመኖሪያ ቤት እጥረት ችግርም ይበልጥ በፈጠራ ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለማግኘት ስሞር ቆይቻለሁ፡፡ እንደ ከተማ እና እንደ ክልላዊ መሪ፣ ጥቅም ላይ የማይውሉ የመንግሥት ንብረቶች መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚያለሙ ድርጅቶች እንዲተላለፉ ግፊት አድርጌያለሁ፤ ከሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ባለሥልጣናት ጋር በመስጠት ክልሉ በቀጣይ አስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ይበልጥ የሥራ ኃይል እና መኖሪያ ቤቶች እንዲገነባ አቋም እንዲይዙ ጥሬያለሁ፡፡ መኖሪያ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ተከራዮችን ምቹ ካልሆነ የመኖሪያ ቤት ሁኔታ ለመጠበቅ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች አስተዋውቄያለሁ፤ በጀት እንዲመደብ አድርጌያለሁ፡፡

ከአልሚዎች ይልቅ ለሰዎች ቅድሚያ ለመስጠት እና ዲሲ በዚህ ለመኖር ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት እንዲሆን ይበልጥ መስራት አለብን፡፡ ለእኔ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡- 

  • ተጨማሪ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን ለመደገፍ የነዋሪው ብዛት ከፍተኛ ሊሆን የሚችልባቸውን አካባቢዎች መፈተሽ፡፡
  • ክፍት ዳውን ታውን የቢሮ ሕንጻዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሊገኙ ወደሚችሉ ለመቀየር ፈጠራ የተሞላበት አካሄድ ለመፍጠር መሥራት፤
  • ይበልጥ ለቤተሰብ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ከአልሚዎች ጋር አብሮ መስራት፤  
  • ለጋራ መኖሪያ ቤት፣ የሕዝብ መንገድ ለመጠቀም እንዲሁም አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለመግዛት ወይም ለመደጎም ፈጠራ የተመላባቸው አካሄዶችን መከተል፤
  • አሁን ላሉ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃ ማድረግ እና የከተማ ገንዘብ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መዋላቸውን ማረጋገጥ፤
  • ሁሉም አከራዮች ተጠያቂነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እና የተከራዮችን ደህንነት በማስጠበቅ ለአነስተኛ አከራዮች ድጋፍ ማድረግ፡፡