ለሁሉም ተማሪዎች የሚሰሩ ትምህርት ቤቶች መፍጠር

ብዙዎቹን ተጋላጭ ተማሪዎቻችንን በሚገባ እያስተናገድን አይደልንም፡፡ በነጭ እና ጥቁር ተማሪዎች መካከል ያለው የዕድል ልዩነት አሁንም ሰፊ ነው፡፡ እንዲሁም በርካታ ወጣቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን የአዕምሮ ጉዳቶች (ትራውማ) በበቂ ሁኔታ ለመፍታት አልቻልንም፡፡ እንዲሁም በክልሉ የተሻሉ ትምህርት ቤቶች ለማግኘት በተለይ ደግሞ በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ በርካታ ቤተሰቦች ከዲሲ እየወጡ በመሆኑ ብዙ ቤተሰቦች እያጣን ነው፡፡

በመሥሪያ ቤት፣ የትምህርት ሥርዓታችን ወጣት ሰዎችን በተሻለ ማገልገል እንዲችል ለማስፋፋት ችለናል፡፡ የሕጻንነት ዘመን ትምህርት ለመላው ዲሲ ተደራሽ እንዲሆን እና ለሕጻንነት ዘመን ትምህርት መምህራን የሚከፈለውን ደመወዝ ለመጨመር ከልደት እስከ ሦስ ዓመት ጽሑፍ በጋራ ጽፌያለሁ፡፡ በተጨማሪም በዙውን ጊዜ ፍላጎቶቻቸው ችላ ለሚባሉ ልጆች እገዛ ለማድረግ ቅድሚያ ሰጥቼ ሰርቻለሁ፡፡ ወላጆች በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የሚሆነውን የማወቅ መብት እንዳላቸው በመረዳት የትምህርት ሥርዓታችንን ግልጽነት እና ገለልተኝነት ለመጨመር ረቂቅ ሕግ አቅርቤያለሁ፡፡ 

ትምህርት ቤቶቻችንን ከማሻሻል አንጻር፣ ሁሉም ነገር በጠረጴዛ ላይ መሆን አለበት፡፡ በትምህርት ቤቶቻችን ለውጥን ለማምጣት የምናደርገው ጥረት የሚመራው ከዚህ በሚከተሉት ይሆናል፡- ውጤታማ ያልሆነውን ለመለየት የትምህርት ሥርዓታችንን ከላይ እስከ ታች መከለስ እና የአሰተዳደሩን መዋቅር መፈተሽ፤

  • ውጤታማ ያልሆነውን ለመለየት የትምህርት ሥርዓታችንን ከላይ እስከ ታች መከለስ እና የአሰተዳደሩን መዋቅር መፈተሽ፤ 
  • ተማሪዎቻችን በዘመናዊ ፋሲሊቲዎች መማራቸውን ለማረጋገጥ እና የግብር ከፋዩ ገንዘብ በውጤታማነት ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ለትምህር እና ለፋሲሊቲዎች ዕቅድ ቁርጠኛ አቋም መያዝ፤
  • ልዩ ልዩ፣ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን የትምህርት ሠራተኞች ይዞ ለመቆየት መምህራን በከፍተኛ ደረጃ ሥራ የሚለቁበትን ሁኔታ መቀየር፤
  • ለተማሪዎች አኩልነት ላይ የተመሠረተ፣ አቃፊ አገልግሎቶች ማቅረብ እና እንደ ነርሶች፣ የቤተመጽሐፍት ሠራተኞች እና አማካሪዎች ላሉት አስፈላጊ ኃብቶች እና ድጋፎች ማቅረብ፤
  • IEP ላላቸው እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎች ተጨማሪ አገልግሎቶች መስጠት፤
  • ተማሪዎች በሙያ ላይ የተመሠረተ ፈቃድ ወይም የምሥክር ወረቀት አግኝተው እንዲመረቁ የሙያ ትምሕርት ዕድሎችን ማስፋት፡፡